የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ክርስቲን ፒሬን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሩ ከአምባሳደሯ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ላይ ተወያይተዋል።
በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ያካሄደው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የፈጠረ በመሆኑ የኔዘርላንድስ ኩባንያዎች እና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ወቅታዊ ሁኔታ፣ በክልላዊ እና ቀጣናዊ የሰላም እና ደኅንነት ዙሪያም ሚኒስትሩ ለአምባሳደሯ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።