ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ

AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጆን ዎጃ ኤሊናና ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ነቢል ማህዲ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጆን ዎጃ ኤሊናና ሁለቱ አገራት በአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ እና በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በዘርፉ የልምድ ልውውጥ እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መወያየታቸው ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ደቡብ ሱዳን የጀመረችውን ሪፎርም እንደምትደግፍ አምባሳደር ነቢል ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ባለስልጣናት በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል አስተማማኝ እና ጠንካራ አየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር እንደሚሰራ ማመልከታቸውን በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review