“ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ሀገር ራስ የመቻል ጉዞዋን በማጠናከር ስሉጥ የሆነ የትውልድ ቅብብሎሽ ማረጋገጥ ይገባታል”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing “ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ሀገር ራስ የመቻል ጉዞዋን በማጠናከር ስሉጥ የሆነ የትውልድ ቅብብሎሽ ማረጋገጥ ይገባታል”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN-የካቲት 26/2017 ዓ.ም

“ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ሀገር ራስ የመቻል ጉዞዋን በማጠናከር ስሉጥ የሆነ የትውልድ ቅብብሎሽ ማረጋገጥ ይገባታል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ ።

ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ቢኖሩም ኢትዮጵያ እስከዛሬ ሶስት አመት በፊት ድረስ ከውጭ በማስገባት ላይ ተመስርታ መቆየቷን አስታውሰዋል።

አሁን ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ የማምረት አልፎም ወደውጭ የመላክ አቅም አሳድጋለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ይህ ርምጃ በምሉዕነት የተገነባ እና በሚገባ የታጠቀ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከማረጋገጥ አንፃር አበረታች ሥራ መሆኑን አውስተዋል።

“ከመከላከያ ግብዓቶች ባሻገር ሀገር የራሷን ምግብ ፣ መድሀኒት እና አልባሳት በበቂ በማምረት እውነተኛ በራስ ምርት መተማመንን ማረጋገጥ ይገባታል” ሲሉም ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review