ኢትዮጵያ ከሃገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለአፍሪካ ብሎም ለሌሎች የዓለም ሃገራት የክትባት ምርት ለማቅረብ ብቁ ናት ፡- ዶ/ር መቅደስ ዳባ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከሃገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለአፍሪካ ብሎም ለሌሎች የዓለም ሃገራት የክትባት ምርት ለማቅረብ ብቁ ናት ፡- ዶ/ር መቅደስ ዳባ

AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የተቀመጡ የክትባት ጥራት ደረጃዎችን በሟሟላት፤ ከሃገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለአፍሪካ ብሎም ለሌሎች የዓለም ሃገራት የክትባት ምርት ለማቅረብ ብቁ ናት ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ክትባት ለማምረት የአዋጭነት ጥናት ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

የመግባቢያ ሰነዱ መፈረም ኢትዮጵያ ክትባትን በሃገር ውስጥ ለማምረት የሚረዳ ትልቅ እርምጃ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የአፍሪካ ሃገራት ክትባትን በራሳቸው አቅም ለማምረት መነሻ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በሃገር ውስጥ ክትባት ማምረት የህብረተሰብ ጤናን ለማረጋገጥ እና ለወረርሽኝ ዝግጁነት ቅድሚያ የሚሰጠው ቁልፍ ጉዳይ ነው ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የተቀመጡ የክትባት ጥራት ደረጃዎችን በሟሟላት፤ ከሃገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለአፍሪካ ብሎም ለሌሎች የዓለም ሃገራት የክትባት ምርት ለማቅረብ ብቁ ናት ብለዋል፡፡

የክትባት ምርት ለመጀመር በቅርብ ወራት የግንባታ እና የምርት ሂደቶችን ለመጀመር ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፤ የአዋጭነት ጥናቱን ለማድረግ ለተመረጠው የህንዱ ቴክኢንቬሽን ላይፍኬር ካምፓኒ ጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቅርብ ወራት የክትባት አምራች ሃገር እንደምትሆን እምነታቸውን የገለጹት የቴክኢንቬሽን ላይፍኬር ካምፓኒ ዳይሬክተር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይድ ኤስ. አህመድ፤ ድርጅታቸው ጥናቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በአግባቡ አጠናቆ እንደሚያስርክብ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የቴክኒክ ቡድን የአዋጭነት ጥናቱን ለሚያደርገው ቡድን የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነቱ በተፈረመበት መድረክ መገጹን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review