AMN- ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበትን ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጌያለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
በውይታችን ወቅት ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበት ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ገልጫለሁ ብለዋል::