ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የ2025 በብሪክስ የግብርና የቴክኒክ ቡድን ስብሰባ ላይ እየተሣተፈች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የ2025 በብሪክስ የግብርና የቴክኒክ ቡድን ስብሰባ ላይ እየተሣተፈች ነው

AMN – መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚሊያ እየተካሄደ የሚገኘው የብሪክስ አባል ሀገሮች የግብርና የቴክኒክ ቡድን ስብሰባ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን እየተሣተፈ ይገኛል።

በስብሰባው በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ የኢትዮጵያ መንግስት ግብርናን ለማዘመን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየተገበራችው ያሉ በርካታ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በተለይም የስንዴ ብሔራዊ ምርት እና በአረንጓዴ ዓሻራ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን አስረድተዋል።

በብሪክስ ማዕቀፍ ግብርና በተለይም የቤተሰብ ግብርና የትብብር መስክ ሊሆን እንደሚገባ እና በዚሁ ረገድ ልምድ በመለዋወጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማሣለጥ እና የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት ማስፋፋት እንደሚገባም መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review