ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምትከተለው ሰላማዊ አካሄድ ተገቢነት እንዳለው ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምትከተለው ሰላማዊ አካሄድ ተገቢነት እንዳለው ተገለጸ

AMN-መጋቢት 22/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የጀመረችው ሰላማዊ ዲፕሎማሲ አካሄድ ተገቢ መሆኑን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በርን ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ ሰላማዊና የዲፕሎማሲ አካሄድ ተገቢነት አለው።

ኢትዮጵያም የባሕር በርን ለመጠቀም ያቀረበችው ጥያቄ አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የሚኖርባት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምትከተለው ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን የባህር በር መሻት ለፍትሕ ቀናዒ የሆኑ የዓለም አገሮች ሁሉ በትክክል ያዩታል የሚል እምነት አለኝ ያሉት አምባሳደር አብርሃም፤ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የተሸከመች ሀገር የባህር በር አጥታ ልትኖር አይገባትም ብለዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄም እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ ለማስተናገድ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

ይህን ሁኔታ የማይረዳ መንግስትም ሆነ አገር ስለማይኖር በሰላማዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ መፍትሔ የሚያገኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የባህር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና የህዝቦቿን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል መፍትሔ ማግኘት እንደሚገባው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review