ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች ነው -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች ነው -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

AMN-የካቲት 8/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በ46 ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎችን በክብር ተቀብላ እያስተናገደች መሆኑንም ተናግረዋል።

እንግዶች ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጀምሮ በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጓን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ መጎልበት ጨምሮ ለአፍሪካ ህብረት መጠናከር ጉልህ ሚና ማበርከቷንና ይህንን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማንሳታቸውን ገልጸዋል።

በተለይ እርስ በእርስ የተባበረና በመሰረተ ልማት የተሳሰረ አህጉር ለመፍጠር ከሌሎች ውንድም እና እህት አፍሪካውያን ጋር እንደምትሰራ መናገራቸውን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያስመዘገበችው ውጤት ለአፍሪካውያን ምሳሌ እንደሚሆን መግለጻቸውንም እንዲሁ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review