የሀገራዊ ለውጡን ሰባተኛ ዓመት ስኬታማ ጉዟችንን እያከበርን ባለንበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት “ልህቀት በሰው ተኮር አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሞክሮ ተኮር ሥልጠና ዛሬ አስጀምረናል።
የኢትዮጵያውያን የዘመናት መሻት የሆነውን የተሳለጠ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት እና በጽኑ መሠረት ላይ ለማኖር የሚያችል ሪፎርም እያካሄድን ነው።
ሪፎርሙ ለአፍሪካ ተምሳሌት የምትሆን፣ የበለፀገችና ጠንካራ ሀገርን ለመገንባት እንዲሁም የህዝባችንን የአገልግሎት ፍላጎት ለማርካት ወሳኝ ሚና አለው።
ይህንን ታሪካዊ ምዕራፍ በማሳካት ዘመን ተሻጋሪና ጠንካራ የመንግሥት የአገልግሎት ሥርዓት ለመዘርጋት ሁሉም የመንግሥት አመራር እና ሰራተኛ በሚጠበቅበት ደረጃ መትጋት ይኖርበታል፡፡
ይህ ተሞክሮ ተኮር ስልጠና የሚካሄደው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓትን ለመገንባት በሚስችሉ በፀደቁ እና በረቂቅ ደረጃ ባሉ ሰነዶች ላይ ነው። በሂደቱም የእስካሁን የሪፎርሙ አፈፃፀም የደረሰበት ደረጃ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችም ላይ ውይይት ይደረጋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ