AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያና ህንድ በልዩ ልዩ ወታደራዊ መስኮች በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በባንጋሎር ከተማ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ በአቅም ግንበታ፣ በመከላከያ ጥናትና ምርምር ፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች፣ በሳይበር ደህነንነት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ይህም የሁለቱን ሀገሮች ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ስምምነቱን የተፈራራሙት በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢንጂነር) ሲሆኑ በህንድ በኩል ደግሞ የህንድ መከላከያ ሚኒስትር ራጃንታ ሲንግ ፈርመዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ህንድ ባዘጋጀችው ኤሮ ኢንዲያ 2025 ላይ በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።