ኢትዮጵያና ስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያና ስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

AMN ግንቦት 28/2017

ኢትዮጵያና ስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ።

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የስሎቪኒያ ፕሬዚዳንት ናታሻ ፒርክ ሙሳር በብሔራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ከስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጋር በአለም አቀፍና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል።

በሁለትዮሽ ጉዳዮች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ስፔስ ሳይንስና ሌሎች ዘርፎች በትብብር በሚሰሩባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን ተናግረዋል።

የስሎቪኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ናታሻ ፒርክ በበኩላቸው፤ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር በምጣኔ ሃብት፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የውሃ አስተዳደርና ሌሎች ዘርፎች በትብብር መስራት የሚፈልጉባቸው እንደሆኑ መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review