AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በመከላከያ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ስር ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አንዱ የሆነውን የኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የመከላከያ ኢንጅነሪግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሃይለማሪያም እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ የመከላከያን ፍላጉት ከማሳካት አንፃር ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸውን የተለያዩ ርቀት ያላቸውን የአጭር የመካከለኛ እና የረጅም ርቀት ራዲዮኖችን ተመልክተዋል።
ሚኒስትሯ የተለያዩ ርቀት ያላቸውን ራዲዮኖች በራሳችን አቅም ማምረት እና መገጣጠማችን እንደ ሀገር ብሎም እንደተቋም በጣም ከፍተኛ የሆነ አቅም እንዳለን የሚያሳይና የሚያበረታታ ነው ሲሊ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።