ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ያለባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት የማጭበርበር ወንጀል ይፈፅም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ያለባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት የማጭበርበር ወንጀል ይፈፅም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN-ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም

ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ያለባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት ገንዘብ ሊያወጡ የሚመጡ ግለሰቦችን የሚረዳ መስሎ ሚስጥር ቁጥራቸውን በማየትና ሌላ ካርድ በመቀየር የማጭበርበር ወንጀል ይፈፅም የነበረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው አለማየሁ የስጋት፣ የወንጀል ድርጊቱን የሚፈፅመው ኤ.ቲ. ኤም ያለባቸው ቦታዎች በመገኘት ገንዘብ ሊያወጡ የሚመጡ በተለይም ደጋግመው የሚሞክሩ ሰዎችን ሲያይ የካርዳቸውን የሚስጥር ቁጥር በማየትና የሚረዳ በመምሰል ካርዳቸውን ወዲያው በሌላ በመቀየር እና ከአካባቢው በፍጥነት በመሰወር ከሌላ ማሽን ገንዘባቸውን አውጥቶ የሚሰወር ነው፡፡

ግለሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል አፈፃፀም ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ፈረንሳይ ማዞሪያ አካባቢ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀኑ7:30 ሠዓት በመገኘት አንዲት ግለሰብ ገንዘብ ለማውጣት ሲሞክሩ ከኋላቸው ሆኖ የካርዱን ሚስጥር ቁጥር ካየ በኋላ የሚረዳ መስሎ በመቅረብ ማሽኑ እምቢ ብሏል እስኪ በሌላ ይሞክሩ በማለት ካርዳቸውን ይዞ ይሄዳል፡፡

ግለሰቧም እውነት መስሏቸው ካርዱን ተቀብለው ደጋግመው ሲሞክሩ የተመለከታቸው የባንኩ ሥራ አስኪያጅ ካርዳቸውን ተቀብሎ ሲያረጋግጥ የግል ተበዳይ አለመሆኑን በማወቁ ተከሳሹ ከአካባቢው ሳይርቅ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review