ኤም ኤን አር ሲ የተባለ ኩባንያ 3 የመንገድ ጠርዝ (curve stone ) መስሪያ ማሽኖችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ድጋፍ አደረገ

You are currently viewing ኤም ኤን አር ሲ የተባለ ኩባንያ 3 የመንገድ ጠርዝ (curve stone ) መስሪያ ማሽኖችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ድጋፍ አደረገ

AMN – ጥር 19/2017 ዓ.ም

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ማሽኖቹ በከተማዋ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት እና ሌሎችም የመንገድ ስራዎች የመንገድ ጠርዞችን በጥራት እና በፍጥነት ለመገንባት ያግዛሉ ብለዋል።

ኤም ኤን አር ሲ ኩባንያ እና ስራ አስኪያጇ ወ/ሮ ማህደር ገብረ መድህን የከተማ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው የተለያዩ የበጎ አድራጎት እና ሰው ተኮር የልማት ተግባራት በንቃት እንደሚሳተፉ ገልጸው በኮንስትራክሽን ዘርፉ በመሠማራትም አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን ከውጭ በማምጣት እና በሀገራችን በማስተዋወቅ ረገድም ሚናቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በመንገድ ስራ እና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ያለውን የመንገድ ጠርዝ መስሪያ ማሽን እጥረት በመመልከት ለከተማ አስተዳደሩ የማሽን ድጋፍ በማድረጋቸው ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች ስንተባበር ሀገርን መገንባት እና ማሳደግ እንችላለን ብለዋል።

ለከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ከተደረጉት የመንገድ ጠርዝ መስሪያ ማሽኖች አንዱ ለዋና መንገድ ጠርዝ መስሪያ የሚያገለግል ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ለአረንጓዴ መናፈሻ ጠርዝ ስራ የሚውሉ መሆኑ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review