ኤቨረስት ተራራ ላይ ሲወጣ ጠፍቶ የነበረ እንግሊዛዊ አካል ከ100 ዓመታት በኋላ ተገኘ

You are currently viewing ኤቨረስት ተራራ ላይ ሲወጣ ጠፍቶ የነበረ እንግሊዛዊ አካል ከ100 ዓመታት በኋላ ተገኘ

AMN-ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

ናሽናል ጂኦግራፊክ ከ100 ዓመታት በፊት ኤቨረስት ተራራ ላይ ሲወጣ ጠፍቶ የነበረን አንድሪው “ሳንዲ” ኢርቫይን የተባለ እንግሊዛዊ ተራራ ወጪ የአካል ክፍልና ጫማ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ኢርቫይን ከ100 ዓመታት በፊት በናሽናል ጂኦግራፊክ በሚመራ አንድ ጉዞ የኤቨረስት ተራራ ጫፍ ላይ ለመውጣት ሙከራ ካደረጉ ሁለት ሰዎች መካከል አንዱ እንደነበር ተገልጿል።

ኢርቫይን ከጆርጅ ማሎሪ ጋር በመሆን በፈረንጆቹ 1924 የአለማችን ረጅሙ ተራራ ኤቨረስት ጫፍ ላይ ለመድረስ ሙከራ አድርጓል፡፡

የቡድን አጋሩ የማሎሪ አስከሬን በፈረንጆቹ 1999 የተገኘ ሲሆን የአንድሪው “ሳንዲ” ኢርቫይን አካል ሳይገኝ ቆይቷል፡፡

ሁለቱ ተራራ ወጪዎች ከመሞታቸው በፊት ወደ ተራራው ጫፍ ደርሰው ይሁን አይሁን የተረጋገጠ መረጃ አልተገኘም፡፡

ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ከተራራው ጫፍ 245 ሜትር ገደማ ርቀት ላይ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review