ኤኤምኤን የህዝብ ድምፅ በመሆን ያከናወናቸውን ተግባራት በማጠናከር ይበልጥ ተመራጭና ተወዳዳሪ ለመሆን እየሠራ ነው- አቶ ካሳሁን ጎንፋ

You are currently viewing ኤኤምኤን የህዝብ ድምፅ በመሆን ያከናወናቸውን ተግባራት በማጠናከር ይበልጥ ተመራጭና ተወዳዳሪ ለመሆን እየሠራ ነው- አቶ ካሳሁን ጎንፋ

AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ባለፉት ጊዜያት የህዝብ ድምፅ በመሆን ያከናወናቸውን ተግባራት በማጠናከር ይበልጥ ተመራጭና ተወዳዳሪ ለመሆን እየሠራ እንደሚገኝ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልፀዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሁሉም የሚወደው እና በባለቤትነት የሚመለከተው ሚዲያ እንዲሆን በተሠሩ ሥራዎች በአሁኑ ወቅት የተደራሽነት አድማሱን ማስፋት ተችሏል ብለዋል፡፡

በይዘት፣ በአቀራረብ እና በቴክኖሎጂ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየው እድገት የሚበረታታ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሚዲያው በህዝብ እና በመንግስት መካከል አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በሰራቸው ሰፊ ሥራዎቹ በህዝብ ዘንድ አመኔታን ማትረፉንም ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ መገኛ በመሆኗ ብዝሀነትን አክብሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ወደ አድማጭ ተመልካች እየደረሰ የሚገኘው ሚዲያው በዚህ ረገድ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ኤኤምኤን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ከማገልገሉም በላይ በተለያዩ ሀገራዊ እና ሰብዓዊ ተግባራት ላይ ተሳትፎውን በማላቅ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ነው ያሉት አቶ ካሳሁን፡፡

ሚዲያው አሁን ለደረሰበት የተወዳዳሪነት ደረጃ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ላቅ ያለ ነበር ያሉት ዋና ሥራ አስፈሚው ለተደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የተቋሙ ሠራተኞች በትብብር መንፈስ ባሳዩት ትጋት እና በአመራሩ ድጋፍና ቁርጠኝነት ጠንካራ አፈፃፀም መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ትብብር እና ቅንጅት ለሚዲያ ተግባር ወሳኝ በመሆኑ በጀመርነው የትብብር መንፈስ መቀጥል ይገባናል ሲሉም ዋና ስራ አስፈጻሚው አሳስበዋል፡፡

ሚዲያው እስከ አሁን አበረታች ተግባራትን ያከናወነ ቢሆንም ቀጣይ ህዝቡን ለማርካት እስከ አሁን ከተሰራው በላይ በእጥፍ መሥራት እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል፡፡

እውነተኛ የሜትሮፖሊታን ሚዲያን ለመፍጠር በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review