እስከ አሁን ድረስ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ አካሄደዋል – ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

You are currently viewing እስከ አሁን ድረስ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ አካሄደዋል – ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 5/2017

እስከ አሁን ድረስ 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የብሔራዊ /ፋይዳ/ መታወቂያ ምዝገባ ማካሄዳቸዉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።

የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀን አፈጻጸም እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ ያለፉት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።

ሚኒስትሩ የዘርፍ አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዲጂታላይዜሽንን በማስፋት እንዲሁም መሰረተ ልማቶች እንዲጠናከሩ በማድረግ በኩል ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ለአብነትም ከገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ 800 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በዲጂታል መንገድ መዘዋወሩን ጠቅሰው፤ ይህም በዲጂታል ስነምህዳር ውስጥ ትልቅ እመርታ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን አንስተዋል።

ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በተያያዘም እስከ አሁን 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ምዝገባ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል።

ይህም ከእቅዱ አንጻር መልካም የሚባል እና በቀጣዮቹ ጊዜያትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።

ከሰው ሀብት ልማት ጋር በተያያዘም በ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ እስከ አሁን 688 ሺህ ኢትዮጵያውያን ተመዝግበው ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review