እንኳን ለ35ኛው የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልካም ምኞች ገለፁ

You are currently viewing እንኳን ለ35ኛው የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልካም ምኞች ገለፁ

AMN – ሰኔ 08/2017 ዓ.ም

የነገ ሃገር ተረካቢ ሕፃናት እናንተ የመጪው ዘመን ተስፋዎች ሁሉም ሥራችን የናንተን የነገ ህይወት መንገድ ለማቅናት የሚደረግ ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ የነገ እደገታችሁ እዳ የሌለበት ነፃ ለትውልድ የሞትተርፍ እንዲሆን ከእቅድ እስከ እለት እለት ትግበራችን ለእናተ እንሰራለን፤ ለዚህ ነው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ያስፈለገን ብለዋል።

የቀዳማይ ልጅነት ሣምንት እና በአፍሪካ ለ35ኛ እንደ ሃገር ለ34ኛ ጊዜ”የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነጽ ሕፃናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን!” በሚል መሪ ቃል ሲከበር ዛሬ አብሪያችሁ ደስታችሁን ስካፈል አሁንም ቀጣይ ስራዎች እንዳሉብን አደራችንን ሳንዘነጋ ነው ብለዋል::

መንግሥት እና ማኅበረሰቡ እናንተ ሕፃናት ለሃገር ያላችሁ ተስፋ እውን እንዲሆን ከማኅፀን ጀምሮ በሚደረግ እንክብካቤ፣ በአልሚ ምግብ፣ በጨዋታ መማር፣ በትምህርት ቤት ምገባ፣ በቤተሰባዊ ትስስር መልካም ዕድገት እንዲኖራችሁ፣ ሁለንተናዊ መብቶቻችሁ እንዲከበሩ፣ በአገራዊ ግንባታ፣ ልማቶች እና ዕድገቶች ውስጥ የእናንተ የሕፃናት ተሳትፎ እንዲረጋገጥ፣ የሕፃናት ፓርላማ እንዲጠናከርና ዴሞክራሲያዊ አሠራር ልምምድ እንዲኖራችሁ እና ለሃገር ተስፋ ያለው ትውልድ እንድትሆኑ መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንደሚባለው ዛሬ የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ እንድትሆኑ አድርገን እናሳድጋችኋለን ፤ አገር ተረካቢ ትውድም ሆናችሁ ትሰራላችሁ ብለዋል::

ከተማችሁ ሀገራችሁ ትወዳችኋለች:: ሁሌም ምርጥ ምርጡን ለናንተ በማለትም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አጋርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review