AMN- ጥር 19/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ይህንን አስመልክተው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፣ “እየሰራን ያለነው ስራ ገና ከጅምሩ በአለም ተወዳዳሪ እያደረገን ነው” ብለዋል።
ለዚህም ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ሲሉ ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ቱሪዝም(UN Tourism) ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሞሮኮንና ግብጽን በማስከተል ባለፉት አምስት አመታት የጎብኝዎች ቁጥር ከነበረበት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።
ከአለም ደግሞ ኳታርን፣ ኤል ሳልቫዶርን፣ አልቤንያን፣ ሳዑዲን እና ኩራካዎን በመከተል ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።