AMN – መጋቢት 7/2017 ዓ.ም
የከተማ ሴፍትኔት እና የስራ ፕሮጀክት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አይዳ አወል፣ ከ23 ሺ አራት መቶ በላይ ዜጎች በከተማ ሴፍትኔት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ በበኩላቸው፣ የከተማ ሴፍትኔት የበርካቶችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ነዉ ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ በመንግስት የሚደገፍ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ለፕሮግራሙ ስኬታማነት አስተባባሪዎች እና የሴፍትኔት ፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በትጋት እንዲሰሩም ጥሪ ቀርቧል።
በተመስገን ይመር