ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በማሳደጊያ ማዕከል ካሳደጋቸው ልጆች መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ በመብቃታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በማሳደጊያ ማዕከል ካሳደጋቸው ልጆች መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ በመብቃታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ

AMN – ጥር- 18/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ከህጻንነታቸዉ ጀምሮ በኮልፌ የወንዶች ልጆች ማሳደጊያ እና በቀጨኔ የሴቶች ማሳደጊያ ማዕከል ካሳደግናቸው ልጆቻችን መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ አብቅተን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ለመፈጸም ያበቃን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ብለዋል::

ሙሽሮቹን እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉት ከንቲባዋ እንኳን ፈጣሪ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ረድቷችሁ ለዚህ ለተባረከ እና ለተቀደሰ የህይወታችሁ ምዕራፍ ቀን እንኳን አደረሳችሁም ብለዋል

የከተማ አስተዳደራችን ወላጅ ለሌላቸዉ ወላጅ እና ቤተሰብ በመሆን አሳድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ከማድረግ በተጨማሪ በቀጣይ የህይወታቸው ምዕራፍ የስራ እድል በመፍጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ዉጤታማ ህይወት እንዲኖራቸው እየተመኘን በዚህ በተቀደሰ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብለዋል በመልእክታቸው፡፡።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review