ከምክር ቤት አባላት ከተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች መካከል፡-

You are currently viewing ከምክር ቤት አባላት ከተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች መካከል፡-

👉ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በመጋፈጥ ወደ ብልጽግና እየሄደች ያለችበት መንገድ የሚደነቅ ነው፡፡

👉ፖለቲካዊ አጀንዳዎችን በንግግርና በውይይት የመፍታት ባህላችን ደካማ ነው፡፡ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተነጋግሮ የመፍታት ባህል መጎልበት ላይ የተሰራ ስራ እና የተገኘው ውጤት ምንድነው?

👉የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ያስገኘው ሰላም እፎይታን የሚሰጥ ነው፡፡በስምምነቱ መሰረት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦች ተግባራዊነታቸው ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

👉በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ወደ ግጭት እንዳያመራ ምን እየተሰራ ነው?

👉የፍትህ ተደራሽነት እና የመልካ አስተዳደር ችግሮችን ለማስተካከል የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸው መልካም ጅማሮ ነው፤ ነገር ግን ከሚታየው ውስበስብ ችግር አኳያ አሁንም የፍትህ ዘርፉ በርካታ ችግሮች የሚነሱበት ነው፡፡ በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ምን እየተሰራ ነው?

👉የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ያለውን የሰላም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው?

👉የዋጋ ንረትን ለመቀነስ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው፤ አሁን ላይ የመንግስት ሰራተኛ እና በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ዜጎች የኑሮ ውድነት ጫና አለባቸው፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ ምን ታስቧል?

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review