ከትንሳኤ በዓል በተያያዘ ምንም አይነት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ገበያዉን ማረጋጋት የሚያስችሉ ተግበራት መከናወናቸዉን የአዲስስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ ተናሩ፡፡
ኃላፊዋ ሀቢባ ሲራጅ የበአል ቅድመ ዝግጅቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ለ2017 ዓ.ም ትንሳኤ በዓል በቂ የምርት አቅርቦት በመፍጠር እንዲሁም ህገወጥ የንግድ አንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር የሚያስችሉ ተግባራት ተከናነዋል፡፡
210 የእሁድ ገበያዎች ፤ 4 የገበያ ማዕከላት፤ የተዘጋጁ ባዛሮች 15 ፤ ከቁም እንሰሳ ማዕከላት 5 ፤ በቂ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የተዘጋጁ መሆናቸዉንም አመላክተዋል፡፡
ከቁም እንሰሳት ጋር በተያያዘም የህብረተሰቡን ፋላጎት መሰረት ያደረጉ የበግ፤ የፍየልና የደልጋ ከብቶችን አቅርቦት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
ማንኛውም ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ሃቢባ ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሰጥ
በ8588 በነፃ ስልክ ጥሪ ላይ መረጃ እንዲሰጥ ማሳሰባቸዉን ከከተማዉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡