ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም አቀባበል አደረጉላቸው

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም አቀባበል አደረጉላቸው

AMN-የካቲት 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለቢሊ ግራሃም ኢቫጀሊካል አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ዛሬ በጽህፈት ቤታቻው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው እና ሁሌ የሚፀልዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እንደጎበኙ እና በአዲስ አበባ ከተማ ባዩት ፈጣን ለውጥም እንደተደነቁ መግለፃቸውን አመልክተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ላሳዩት ፍቅር እና መልካም ምኞትም ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review