ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ የመኖሪያ ህንጻዎችን መርቀው ለነዋሪዎች አስተላለፉ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ የመኖሪያ ህንጻዎችን መርቀው ለነዋሪዎች አስተላለፉ

AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የበጎነት መንደር በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ የመኖሪያ ህንጻዎችን መርቀው ለነዋሪዎች አስተላለፉ።

በምረቃው ላይ ከተባበርን ሀብት አላጣንም ብዙ መስራት እንችላለን በዚህም የብዙዎችን ህይወት መለወጥ እንችላለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ መሰረተ ልማት ለማሟላት ብቻ ሳይሆን የዜጎችንም ህይወት ለመለወጥ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ይህንን ተግባር የምናከናውነው ግን በመንግስት በጀት ብቻ ሳይሆን በልበ ቀና ባለሀብቶች ትብብር ጭምር ነው ብለዋል።

ልማታችን አካታች ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በከተማዋ ልማት ማንም ወደ ኋላ እንዳይቀር በማድረግ ማህበራዊ ፍትህን እናሰፍናለንም ሲሉ ተናግረዋል።

በበጎነት መንደር 7 ህንጻዎችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 5 ህንጻዎችን መገንባት ችሏል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በከተማዋ የነዋሪዎችን ህይወት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት በበርካታ መስኮች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች ለድጋፉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review