ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን የህጻናት የአንጎል እና ህብረሰረሰር ቀዶ ህክምና ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን የህጻናት የአንጎል እና ህብረሰረሰር ቀዶ ህክምና ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

AMN- የካቲት14/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን እና በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባውን የህጻናት የአንጎል እና ህብረሰረሰር ቀዶ ህክምና ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ።

ማዕከሉ ለከተማችን ብቻ ሳይሆን በሪፈር ወደ ከተማዋ ለሚመጡ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ህጻናት ሁሉ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ የያዝነውን ራዕይ ለማሳካት በሁሉም መስክ ነው መስራት ያለብን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጫዎቻ ስፍራዎች ፣ አልሚ ምግብ እና ትምህርት ከሟሟላት ባሻገር ሲታመሙ ለማከምም ደረጃቸውን የጠበቁ የጤና ማዕከላትን በማሟላቶ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

የዘውዲቱ ሆስፒታል የህክምና የልህቀት ማዕከል እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች በሆስፒታሉ ማስፉፊያ እየተገነባ ያለው ዘመናዊ ህንጻ ዘመኑን የዋጀ የህክምና መሳሪያዎች ጭምር ተሟልተውለት ወደ አገልግሎት ሲገባ የሚሰጠው አገልግሎትም ከፍ እንደሚል ገልጸዋል።

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባውን የህጻናት የአንጎል እና ህብረሰረሰር ቀዶ ህክምና ማዕከል ሪች አናዘር ፋውንዴሽን በተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም 400 ሚሊየን ብር ገደማ በሆነ ገንዘብ የውስጥ መሳሪያዎቹ ተሟልተውለት የተቋቋመ ነው።

64 አልጋዎች፣ ዘመናዊ መሳሪያ የተሟላላቸው 2 የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍሎች ፣2 የጽኑ ህሙማን ክፍሎች፣ የተመላላሽ ህክምና ፣የብቻ የማጥቢያ ፣ የአስታማሚ እንዲሁም የህጻናት መጫወቻ ምቹ ክፍሎችን ያሟላ መሆኑ ተገልጿል።

በአመት 5 ሺህ ለሚደርሱ ህጻናት የህክምና አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው ማዕከሉ በዘርፉ ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ለማፍራት የልህቀት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ተብሏል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review