ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር መወያየታቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር መወያየታቸዉን ገለጹ

AMN- ግንቦት 17/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ የተለያዩ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በየደረጃው ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ሲካሄድ የቆየው 4ኛ እና የማጠቃለያ መድረክ በሆነው በዚህ ውይይት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ እያደረጉ ያሉ በርካታ የልማት ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎቻችን ግልጋሎት ክፍት እንድናደርግ፤ ህፃናት ተመግበዉ፣ ተመሳሳይ ዩኒፎርም ለብሰው እና የትምህርት ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው እንዲማሩ ያገዙንን ግብር ከፋዮቻችንን አመስግነናል ብለዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እና ዘመናዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ዝርጋታ፣ የአሰራር ስርዓት በማዘመን፣ በአንዳንድ ፈፃሚዎቻቻንም ሆነ ነጋዴዎች ዘንድ የሚታዩ የስነ ምግባር ጉድለቶችን ማረም እንዲሁም የፈፃሚዎችን አቅም በማሳደግ ረገድ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ ለማላቅ በቅርበት አብረን ለመስራት ተግባብተናል ሲሉም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review