ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ ከማይመቹ ካምፖች ለተነሱ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት መኖሪያ ቤቶችን አስተላለፉ

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ ከማይመቹ ካምፖች ለተነሱ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት መኖሪያ ቤቶችን አስተላለፉ።

አዲስ አበባን ውብ እና ጽዱ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራ ቅድሚያ የነዋሪውን ህይወት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ካምፖች ሲኖሩ የነበሩ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የተሻለ ኑሮ ለመኖር እንዲችሉ ቤቶች እንዲሰጧቸው መደረጉን ተናግረዋል።

ከካዛንቺስ አካባቢ የኮሪደር ልማት ብቻ የተነሱ 340 የአዲስ አበባ ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የሪፕብሊካን ጋርድ አባላት የቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጋቸው ተገልጿል።

ምቹ ካልሆኑ ካምፖች እንዲነሱ የተደረጉት ከእነዚህ የፖሊስ አባላት ውስጥ ቤተሰብ የመሠረቱት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የቤት ተጠቃሚ መደረጋቸውም ተገልጿል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review