AMN – ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሌት ከቀን በመስራት ላይ የሚገኙ ብርቱ ሰራተኞቻችን፣ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪዎችን እና የመንግስት ተቋማት አስተባባሪዎችን በማመስገን በጋራ አክብረናል” ብለዋል፡፡
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ “በኮሪደር ልማት የስራ እድል አግኝታችሁ በታማኝነት እና በትጋት ሌት ከቀን በመስራት ላይ ለምትገኙ ብርቱ ሰራተኞቻችን ሁሉ ዛሬ እናንተ የጣላችሁት መሠረት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ደማቅ ታሪክ በመሆኑ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል::