ከአዲስ አበባ ከተማ የተወጣጡ መምህራን እና ተማሪዎች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከልን ጎበኙ

You are currently viewing ከአዲስ አበባ ከተማ የተወጣጡ መምህራን እና ተማሪዎች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከልን ጎበኙ

AMN – የካቲት 28/2017 ዓ.ም

ከአዲስ አበባ ከተማ የተወጣጡ መምህራን እና ተማሪዎች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገውን ግዙፉ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬሽን ማዕከል በዛሬው ዕለት መምህራን እና ተማሪዎች ጎብኝተውታል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ ማዕከሉ የፈጠራ ክህሎትን በማሳለጥ የሀገራችንን ተወዳዳሪነት በዓለም አደባባይ የሚያረጋግጥ መሆኑን እና አዲሱ ትውልድም አዲስ አስተሳሰብ እና ፈጠራዎችን ለተቋሙ በማበርከት የራሱን አስተዋፅዖ ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review