
AMN – ታኅሣሥ 15/2017 ዓ.ም
ክፍለ ከተሞች በሌማት ትሩፋትና በስራ ዕድል ፈጠራ ያሳኩትን ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመለከተ ፡፡
የስራና ክህሎት ቢሮ የሌማት ትሩፋትና የስራ እድል ፈጠራ የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩም በሌማት ትሩፋትና በስራ እድል ስራ ላይ የመጡ ለውጦች ስለመኖራቸው ያነሱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ያክል በተደረገው ግምገማ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች አሉ ለዚህ የተሻለ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።
ባለፉት 43ቀናት በነበረው የሌማት ትሩፋትና የስራ እድል ፈጠራ ላይ የተገኙ ለውጦችን በማስቀጠል ለድክመቶቹም ኃላፊነት መውሰድና ለሚቀጥለው የተሻለ ስራ ለመስራት መትጋት እንደሚገባ ተመልክቷል።
ክፍለ ከተሞች በሌማት ትሩፋትና በስራ ዕድል ፈጠራ ያሳኩትን አጠናክረው በማስቀጠል እንደክፍተት የታዩትንም በውጤት ለመቀየር በትጋት እንደሚሰሩ ከየክፍለ ከተሞቹ ና ወረዳዎች የተሳተፉ አመራሮች ገልፀዋል።
በግምገማው የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በፅዮን ማሞ