ኮሚሽኑ የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ የሚሳተፉበት መድረክ ሊያካሂድ ነው

You are currently viewing ኮሚሽኑ የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ የሚሳተፉበት መድረክ ሊያካሂድ ነው

AMN – ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ የሚሳተፉበት መድረክ ለማካሄድ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በውይይቱ ለሚሳተፉ በሀገር አቀፍ እና በፌዴራል ደረጃ ለሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አካላት፣ ወዘተ ጋር ውይይት ለማድረግ ጥሪ እያደረገ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ በሂደቱ ላይ አካታችነትን እና አሳታፊነትን ከማጎልበት አንፃር፣ ከዚህ ቀደም በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ከለያቸው ባለድርሻ አካላት በተጨማሪ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኘውም ገልጿል፡፡

በውይይቱም ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎሉ አጀንዳዎች እንደሚቀርቡ እንደሚጠበቅ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተቋማት በውይይት ሂደቱ እንደሚሳተፉ ከኮሚሽኑ የማህበራዊ የትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

1. የፌዴራል መንግስት ስራ አስፈጻሚ

2. የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

3. የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት

4. የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች

5. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

6. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

7. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

8. ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች

9. የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት

10. የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

11. የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን

12. የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን

13. የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

14. የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም

15. የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

16. የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን

17. የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማህበር

18. የሴቶች ጥምረት ለምክክር

19. የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን

20. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን

21. የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

22. የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች

23. ማህበራዊ አንቂዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች

24. የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት

25. የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

26. የፌዴራል ሲቪል ማህበራት

27. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ካውንስል

28. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር

29. የፌዴራል የሙያ ማህበራት

30. የቀድሞ የፖሊስ፣የመከላከያ ሰራዊት

31. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

32. የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

33. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

34. ኮሚሽነሮች (ከተለያዩ ተቋማት)

35. ተፅእኖ ፈጣሪና ታዋቂ ግለሰቦች

36. የፌዴራል የዩኒቨርሲቲ ተቋማት

37. የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የእድሮች ማህበራት ጥምረት

38. የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ናቸው

ኢትዮጵያ እየመከረቾ ነው!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review