AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም
ወጣቶች ስራን ከማማረጥ ጎጂ ልማድ ተላቀው በሁሉም መስክ ሀገርን ለመጥቀም እንዲተጉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡
ከንቲባዋ ባለፉት ስድስት ወራት በብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ሲያደርጉ የቆዩ 13 ሺህ 527 ሴቶችና ወጣቶችን አስመርቀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከ142 ሺ በላይ ቋሚ የስራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል።

በኮሪደር ልማት ስራ ደግሞ ከ70 ሺ በላይ ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸውም ነው ያነሱት።
ዜጎች ስራን ከማማረጥ ጎጂ ባህል በመላቀቅም በሀገራቸው ሰርተው ለመለወጥ እንዲተጉም ጥሪ አስተላልፈዋል።
የከተማ አስተዳደሩም በስልጠና ፣ ፋይናንስ እና የመስሪያ ቦታን በማመቻቸት ያግዛልም ነው ያሉት።
የአለም ባንክ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር እየተሰጠ ባለው ልምምድ በሁለተኛ ዙር ከተሳተፉት ከ13 ሺህ በላይ ዜጎች ከ99 በመቶ በላይ ቋሚ ስራ አግኝተዋል።
በሶስተኛው ዙር ደግሞ ከሁሉም ክፍለከተሞች 15 ሺ ዜጎች እንደሚሳተፉም ተጠቅሷል።
በአፈወርቅ አለሙ