AMN – ጥር 9/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የከተማዋ ወጣቶች የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ሃይማኖታዊ እሴታቸውን ጠብቀዉ እንዲከበሩ ለማድረግ ሚናቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቀረበ
የቢሮው ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በዓላቱ ሃይማኖታዊ እሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ ከከተማዋ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር ምክክር አድርገዋል ::
ሃላፊው በዓሉ ከሃይማኖታዊ እሴትነቱ ባሻገር በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሀብት መሆኑን አስታውሰዋል ።
የከተራና የጥምቀት በዓል የአብሮነትና የወንድማማችነት ማሳያ በመሆኑ በአሉ ይህን እሴት ጠብቆ እንዲከበር ወጣቶች የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡም አቶ በላይ ጥሪ አቅርበዋል።
ማህበራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ የቱሪዝም መስህብነቱም እንዲጨምር የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንወጣለን ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶች፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ