“ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የዓለም ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት ይገባል” – ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር)

You are currently viewing “ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የዓለም ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት ይገባል” – ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዚያ 01/ 2017

የ150ኛው ዓመት የዓለም ፓርላሜንታዊ ሀገራት ህብረት (IPU) በኡዝቤክስታን ታሽከንት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባል ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ‘የነገን የአለም መሪዎችን ማፍራት’ /cultivating the next Generation of Global leaders/ በሚል ርዕስ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወጣቶችን ያላማከለ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚያዊ ሥርዓት ቀጣይነት እንደማይኖረው ገልፀው በተጨባጭ የወጣቶችን ተሳትፎና ሚና ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ወጣቶች የነገ መሪዎች መሆናቸው እንዲረጋገጥ ወጣቶችን በቴክኖሎጂ አቅም መገንባት፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ማሳደግ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነም ተናግረዋል።

ሁሉም ሀገራት ለወጣቶች የበለጠ ትኩረት በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በተጨባጭ በሚገለጽ ደረጃ የወጣቶችን ተሳትፎ ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ወጣቶችን ለማብቃት እያደረገች ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸው “5 ሚሊዮን ወጣት ኢትዮጵያውያን ኢንኮደሮች” ፕሮግራም ወጣቶችን ለማብቃት ተጨባጭ ምሳሌ እንደሆነ ለጉባዔው ገልፀዋል፡፡

ይህም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በደቡባዊው የዓለማችን ክፍል ለሚገኙ በቴክኖሎጂ እድገት ላልበለፀጉ ሀገራት በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚችል ትልቅ እርምጃ እንደሆነ መግለጻቸዉን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review