AMN-ጥር 18 /2017 ዓ.ም
የጤና ሚኒስቴር ከአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር “የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ እናትነት” በሚል መሪ ሀሳብ የእናትነት ወርን ምክንያት በማድረግ ወርሃዊ የጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄዷል፡፡
በመርሀ ግብሩ የጤና የሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዜጎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማጎልበት ራሳቸውን ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ሊጠብቁ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የእናትነት ወርን ምክንያት በማድረግ ዛሬ የተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ከቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ እስከ አለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል የእግር ጉዞ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል፡፡