የ5ኛ ዙር የኤፍኤ ካፕ የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

You are currently viewing የ5ኛ ዙር የኤፍኤ ካፕ የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

ምሽት 4ከ30 ላይ በሲቲ ግራውንድ ኖቲንግሀም ፎረስት ኢፕሲውች ታውንን ያስተናግዳል።

ሁለቱ ክለቦች በኤፍኤ ካፑ ለ4ኛ ግዜ የሚገናኙ ሲሆን፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ሁለቱን ማሸነፍ ችሏል።

ክለቦቹ በተገናኙባቸው ያለፉት 15 ጨዋታዎች ኢፕሲውች ከሜዳው ውጭ አሸንፎ አያውቅም።

ኢፕሲውች በታሪኩ ለ5ኛ ዙር ሲደርስ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ 2006 ላይ በዋትፎርድ ተሸንፎ ከውድድሩ መሰናበቱ ይታወሳል።

1993 የውድድር ዓመት ደግሞ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

በአልማዝ አዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review