የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲያካሂድ የቆየዉን የአጀንዳ መለየት ሂደት አጠናቀቀ

You are currently viewing የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲያካሂድ የቆየዉን የአጀንዳ መለየት ሂደት አጠናቀቀ

AMN – ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም

ኮሚሽኑ ከተለያዩ የህብረሰብ ከፍል ተወካዮች እና ከባለድርሻ አካላት የተሰበሰቡ ሀገራዊ አጀንዳዎችንም በይፋ ተረክቧል ።

በክልሉ ከሚገኙ 12 ዞኖች እና 96 ወረዳዎች የተዉጣጡ 2 ሺህ ተወካዮችን በማሳተፍ ለሶስት ቀናት በቆየዉ የዉይይት ሂደት ላይ አጀንዳዎች የመለየት እና ለቀጣዩ ዉይይት ህብረተሰቡን የሚወክሉ ተወካዮችን የመምረጥ ሂደትም በስኬት ተከናዉኗል ።

የባለ ድርሻ አካላት እና ቁጥራቸዉ 80 የሚሆኑት የህብረተሰብ ተወካዮችም የጋራ ያደረጓቸዉን 38 የሚደርሱ አጀንዳዎች በማሰባሰብ ለኮሚሽኑ አስረክበዋል ።

የባለ ድርሻ አካላቱ 12ቱ የፖለቲካ ፓርቲ ፣ የሲቪክ ማህበራት ፣ የመንግስት አካላት ፣ የሀይማኖት ተወካዮች እንዲሁም ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችም ተወካዮቻቸዉን መርጠዋል።

የህብረተሰብ ክፍሉን የወከሉት 80 ተወካዮች እና የባለ ድርሻ አካላቱን የወከሉት ተወካዮች በቀጣይ በሚካሄደዉ ዋናዉ ሀገራዊ መክክር ሂደት ላይ ክልሉን የሚወክሉ መሆናቸዉን ከኮሚሽኑ የተገኘዉ መረጃ ያሳያል።

ሂደቱም አሳታፊ ፣ ተአማኒና ነጻ ከመሆኑ ባሻገር ህብረተሰቡ ችግሩን በዉይይት የመፍታት ዴሞክራሲያዊ ሂደትን የተገበረበት እንደነበርም ተመላክቷል።

በአለማየሁ አዲሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review