AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም
የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ድርድሮች ከሃገራችን ብሄራዊ ጥቅም አንጻር ካላቸው አንድምታ መቃኘት እንዳለባቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያን ሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሮችን እንዲያደርግ ኃላፊነት የተሰጠው ብሔራዊ ተደራዳሪ ኮሚቴ እያከናወናቸው ያሉት ተግባራት ገምግመናል ብለዋል፡፡
በየደረጃው የሚደረጉ ድርድሮች ከአገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም እና ከማክሮ ኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ጋር ያላቸውን መናበብ መገምገማቸውንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡