የሃገራችንን የግብይት ስርዓት ከመሰረቱ የሚቀይር የበየነ-መረብ ግብይት አስጀምረናል፡ ካሳሁን ጎፌ ( ዶ/ር )

AMN- ጥር 15/2017 ዓ.ም

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ( ዶ/ር ) በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የበለጸገና የሃገራችንን የግብይት ስርዓት ከመሰረቱ የሚቀይር የበየነ-መረብ (ኦንላይን) ግብይትን ማስጀመራቸውን ገለፁ፡፡

አዲሱ የግብይት ስርዓት የንግዱ ዘርፍ በሃገራችን ኢኮኖሚ የሚገባው ድርሻ እንዲወጣ ያስችላልም ብለዋል፡፡

ዶክተር ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የበየነ-መረብ ግብይት ስርዓት ፍትሃዊነትን የሚያረጋግጥና ለወጪ ንግዳችን ብዝሃነት ትልቅ ግብዓት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር ከደላላ የጸዳና አምራችና ነጋዴ ከያሉበት በቀጥታ የሚገናኙበት ስርዓት ነውም ብለዋል፡፡

ከንግዱ ማህረሰብና ከመላው ህዝባችን በመተባበር የግብይት ስርዓታችንን በማዘመን አርሶ አደሮች የአካታች የፋይንስ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑም ለሚሰራው ስራም አጋዥ ይሆናልም ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሆኑ አስራሮችን በሃገራችን በማስጀመር ፈጣንና አካታች ኢኮኖሚን ለማሳካትም ያግዛል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የዲጂታል ግብይትን ጽንሰ ሀሳብ ያነገበ አዲሱን የኢትዮያ ምርት ገበያ መለያ ምልክት (ሎጎ) ይፋ መደረጉን አመልክተዋል፡፡

በሌላ ሁነት ደግሞ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን ባለ 24 ወለል ህንጻው በአዲስ አበባ ሜከሲኮ አካባቢ የሚገነባ ነው፡፡

የህንጻው ግንባታ የአጠቃላይ የለውጥ ፓኬጁ አካል ሲሆን ሲጠናቀቅ ለቀልጣፋና አካታች ግብይት ምቹ የስራ ከባቢን የሚፈጥር ሲሆን ለተጀመረው የዲጂታል ገበያ ስርዓትም ትልቅ ግብአት አለው ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review