AMN – ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባ በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡
ምክር ቤቱ በስብሰባው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ሰኔ 13 / 2ዐ16 ዓ.ም ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ እንደሚታወስ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡