የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል እየተከበረ ይገኛል

You are currently viewing የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል እየተከበረ ይገኛል

AMN – መስከረም 25/2016 ዓ.ም

የ2017 ዓ.ም ሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ ስነ ስርዓት የተጀመረው በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት ነው።

የበዓሉ ተሳታፊዎች ከሌሊት ጀምሮ ወደ ስፍራው በማቅናት ነው በዓሉን እያከበሩ የሚገኙት።

ወጣቶች በባህላዊ አልባሳት ተውበው በቡድን ባህላዊ ዜማዎችን በማቅረብ በዓሉን እያከበሩ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆረ ፊንፊኔ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ ላይም ይገኛሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review