የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን እየጎበኙ ይገኛሉ

You are currently viewing የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን እየጎበኙ ይገኛሉ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከተመረቀ ጀምሮ የተለያዮ አካላት እየጎበኙት ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለትም ማዕከሉን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች እየጎበኙት ይገኛሉ። በማዕከሉ ባዩት ነገር ጎብኝዎች መደሰታቸውንና መገረማቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ማዕከሉ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ከማበረታታትና ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ከማድረግ ባሻገር፤ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ከማሳደግ አኳያ የሚኖረው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል 40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች ይገኙበታል።

በማዕከሉ የሚገኙ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን የሚያስተናግድ እያንዳንዳቸው ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው 2 ትላልቅ አዳራሾች፣ 8 አነስተኛ እና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሾች በጠቅላላ እስከ 10 ሺሕ ሰዎችን መያዝ ይችላሉ።

ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራና ሁለት አንፊ ቴአትር፣ 2 ሄክታር የዉጪ ኤግዚቢሽ ቦታ፣ ሁለት ሞሎች ይገኙበታል።

ሬስቶራንቶች፣ በርካታ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያካተተ በሀገራችን ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል ነው።

በከተማችን ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው ባሻገር፤ የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራ በአጠቃላይ እስከ 2 ሺሕ መኪናዎችን የማቆም አቅም ያላው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review