የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ በምክር ቤቱ አባላት ከተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል፡-

You are currently viewing የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ በምክር ቤቱ አባላት ከተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል፡-

✍️ገዢ ትርክቶቻችንን የሚፈታተኑ ብልሹ አሰራሮችን ለማረም እና ለማስተካከል ምን እየተሰራ ነው?

✍️ከኢንቨስትመንት መሬት አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያሉ ብልሹ አሰራሮች እንዴት ይታረማሉ?

✍️በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል፣ በ2017 በጀት ዓመት 8.4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ በእቅድ ተቀምጧል፡፡በበጀት ዓመቱ ለመስራት የታቀዱ ዝርዝር ጉዳዮች ምንድናቸው?

✍️መለያየትና ጥላቻን እየሰበኩ ሀገርን የማፍረስ አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች አሉ፡፡ ሰላማዊ መፍትሄ እና ህግ የማስከበር ስራ እንዴት ተጣጥሞ ይጓዛል?

✍️የሀገር ውስጥ የታክስ ገቢን ማሳደግና የመንግስት ወጪን ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል የተሻለ ውጤት ቢመዘግብም የታክስ ገቢ በተፈለገው መጠን አላደገም፡፡

በ2017 የመንግስት ገቢን በከፍተኛ መጠን ለመጨመር አቅዷል እንዴት ተግባራዊ ይደረጋል?

✍️የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ ከመደረጉ በፊት በኢኮኖሚያችን ላይ የነበሩ ችግሮችን ምን ነበሩ?

✍️የሀገራችን የፋይናንስ ዘርፍ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሁሉም የአገልግሎት መስኮች ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡የፋይናንስ ዘርፍ የእስካሁን አፈጻጸምን ቢያብራሩልን?

✍️የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር በተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ የተፈጠረውን አላስፈላጊ የዲፕሎማሲ ውጥረት ለማርገብ እና የሀገሪቱን ገጽታ ለማጠልሸት የሚካሄደውን ዘመቻ የማክሸፍ ስራ መሰራቱ ተገልጿል፡፡ተግባራቱ ምንድናቸው? ያመጡት ውጤትስ?

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review