AMN- የካቲት- 11/2017 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን እያካሄደ ባለው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀም እያዳመጠ ይገኛል።
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያከናወናቸው ተግባራት እንደሚቀርቡ እና ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ አስረድተዋል።
የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለን የኮሚሽኑ ሪፖርት እንዲቀርብ በጋበዙት መሰረት፣ ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እየቀረበ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።