AMN – የካቲት 4/2017 ዓ.ም
የክልሉ ኮሪዶር ልማት በሁለት ምእራፍ በ7 የክልል ማዕከል ከተሞች የሚከናወን መሆኑ ተመልክቷል፡፡
እነዚህም ሆሳዕና፣ቡታጅራ፣ወራቤ ወልቂጤ፣ዱራሜ ቁሊቶ እና ሳጃ ከተሞች ናቸው ተብሏል፡፡
የኮሪደር ልማቱ የሚያካትታቸው ሥራዎች የእግረኛ መንገድ፣የዉኃማ አካላት ልማት፣ፓርኪንግና ፋውንቴኖች፣ሕዝባዊ ኩነት ማካሄጃ ቦታዎች፤የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ፕላዛዎችና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን ማካተቱም ተገልጿል፡፡
በተከታታይ የምሰል አቅርቦቱ ዐሥረኛው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡