የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ከተማዋን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ገለጸ፡፡
ፅህፈት ቤቱ የ2017 በጀት አመት የቅንጅታዊ ፎረም 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤ እቅድ አፈፃፀሙን ግምገማ አካሂዷል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበት መሆኑን በቢሮ ሃላፊ ደረጃ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ገልጸዋል፡፡
በተለይም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሲቪል ምዝገባ፣ በአደጋ መከላከል እና የከተማዋን ውበት በማስጠበቅ በኩል በቅንጅት ለውጦችን ማስመዝገብ እንደተቻለ ተመላክቷል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በቅንጅታዊ አሰራሮች የተገኙ ውጤቶች ለሌሎችም ከተሞች ተሞክሮ ሊሆኑ እንደሚችሉ አቶ ተፈራ አመላክተዋል፡፡
በሩዝሊን ሙሐመድ