የምስራቅ ዕዝ ሬጅመንት ህገ ወጥ ጭነት የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች መያዙን አስታወቀ

You are currently viewing የምስራቅ ዕዝ ሬጅመንት ህገ ወጥ ጭነት የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች መያዙን አስታወቀ

AMN – ጥር- 18/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ሰማድዮ በሚባል አከባቢ ሶስት ቀን የፈጀ አሰሳ ያደረገው ሬጅመንቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታውቋል።

የክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል በቃኽኝ ከተማ ሬጅመንቱ ባደረገው እልህ አስጨራሽ የቀን እና የማታ አሰሳ በሃገር እና እዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችሉ የነበሩ የኮትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።

መቶ አለቃ ቶፊቅ አሊ ሬጅመንቱ 18 ኮትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ማለትም እንደ አሽሽ ፣ መድሃኒት ፣ የመኪና መለዋወጫ ፣ ሲጋራ እና ቦንዳ ጨርቆችን ጨምሮ የተለያዩ ባሃገር ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ በአጠቃላይ 33 ተሽከርካሪ እገ ወጥ እቃዎችን የያዘ ሲሆን አዋሽ ለሚገኘው የጉምሩክ ቅርንጫፍም ማስረከቡን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አመልክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review