የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፋሲካ በዓልን አስመልክተው ከዩክሬን ጋር ላለው ጦርነት የተኩስ አቁም አወጁ

You are currently viewing የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፋሲካ በዓልን አስመልክተው ከዩክሬን ጋር ላለው ጦርነት የተኩስ አቁም አወጁ

AMN-ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፋሲካ በዓልን አስመልክተው ከዩክሬን ጋር ላለው ጦርነት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አውጀዋል።

የተኩስ አቁሙ ከቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰዓት እስከ እሁድ እኩለሌሊት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዩክሬን የተኩስ አቁም ውሳኔውን እንደምትቀበል ያላቸውን እምነት የገለፁት ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ ወታደሮች ማንኛውንም ጥሰት ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ዩክሬን የተኩስ አቁሙን መቀበል አለመቀበሏ ግልፅ አለመሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review