AMN-የካቲት 5/2017 ዓ ም
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ድርድሩ በሚጀመርበት እና ጦርነቱ በሚቋጭበት ሁኔታ ላይ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚን ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገልጸዋል።
ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ተስፋ ሰጪ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ኘሬዝደንት ፑቲንም ሆኑ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ጦርነቱ እንዲቆም ይፈልጋሉ ብለዋል።
ከኘሬዝደንት ፑቲን ጋር ስላደረጉት መልካም ውይይት ለፕሬዝደንት ዘለንስኪ እንደሚገልጹላቸውም ትራምፕ ገልጸዋል ።
የሩሲያና ዪክሬን ድርድር በቅርቡ እንደሚጀምር ገልጸው ድርድሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው እንደሚመሩትም አመልክተዋል ።
ሁለቱ ወገኖች ከስምምነት ላይ ደርሰው ውድመት እያስከተለ የሚገኘው ጦርነት እንደሚያበቃም ተስፋቸውን መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።